הקס

ቄስ፣ ተዋጊው እና አምስቱ ህዋሳት

እውነታውን የሚቀይሩ ትምህርቶች እና አውደ ጥናቶች

የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ቅርሶች እና ትክክለኛውን ባህል ለመላው የእስራኤል ህዝብ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ ዘረኝነትን መቀነስ፣ በእስራኤል ህብረተሰብ መቻቻልን ማጠናከር እና አንዱ ሌላውን የመቀበል ማህበራዊ አቅም ማዳበር እንደሚቻል እናምናለን፡፡

ስለ እኛ ጻፈ

የፕሮጅርክቱ ግቦች ምንድን ናቸው?

ቅርሶችን

በእስራኤል ህብረተሰብ ውስጥ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እሴቶች እና ቅርሶችን ማዋሃድ፡፡

አመለካከቶች ማስወገድ፡፡

ስለ ኢትዮጵያ ይሁዎች የአሉትን የተሳሳቱ አመለካከቶች ማስወገድ፡፡

ማበልፀግ፡፡

ተሳታፊዎችን በኢትዮጵያ ይሁዲዎች እሴቶች፣ ባህሎችና ቅርሶች ማበልፀግ፡

ወግ በሰነድ መዝግቦ ማቆየት፡፡

የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባህልና ወግ በሰነድ መዝግቦ ማቆየት፡፡

ትምህርቶች እና የግል ታሪኮች

የግል የሕይወት ታሪኮች እና ወደ እስራኤል ለመግባት የተደረገውን የጉዞ ታሪክበኢትዮጵያ ሲኖሩ በነበሩ፣ የጉዞው ስቃይ በአሳለፉ እና ወደ እስራኤል ምድር እስኪደርሱ ድረስ የጉዞውን አስቸጋሪ ውጣ ውረድ ባሳለፉ ሰዎች እናቀርባለን

ከኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባህል እና ታሪክ ጋር የሚያስተዋውቁ ትምህርቶችን እንሰጣለን ፡፡

ስለ ስግድ በዓል፡ መነሻ የትምህርት ንግግር፡፡ በኢትዮጵያ ስለ ነበረው አከባበር የግል ታሪክ፣ስለ በዓሉ ወግ እና ደምብ እንዲሁም ድሮ እንዴት ሲከበር እንደነበር እና ዛሬ እንዴት እንደሚከበር ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

በሱዳን ለሞቱ የመታሰቢያ ሐውልት ላይ የሚተረክ የግል ታሪክን የሚያጣምሩ ጉብኝቶች አሉ ፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ማህበረሰብ ፀሎት ቤት የሚያስቃኝ ጉብኝት አለ ፡፡

አውደ ጥናቶች እና እንቅስቃሴዎች

የሸክላ ቁሳቁሶች ዝግጅት

የተለያዩ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን በሸክላ ማዘጋጀት። በዝግጅቱሂደት የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ከእጅ ስራ ጋርያላቸውን ታሪካዊ ይዘት በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

ባህላዊ ጎጆ ቤት መገንባት

ፕሮጀክታችን ልክ በኢትዮጵያ የገጠር መንደሮች የሚሰሩ የጎጆ ቤቶን የመስራት ልዩ ልምድ እንዳለ ስንገልፅ ኩራት ይሰማናል፡፡ የጎጆ ቤት ባህላዊ መኖሪያ ሲሆን በተለይም በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች የተለመደ ነው፡፡ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ይሁዲዎች በዚህ ዓይነት ቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ምግብ ትውውቅ

የዳቦ እና አንጅራ ዝግጅትን ጨምሮ በልዩ ንጥረ ነገሮች የተዋህደ ባህላዊ ምግብን ማዘጋጀት እና በመጨረሻም የተዘጋጀውን ምግብ መቅመስ፡፡

סיור ואירוח בקרית גת

በክሪያት ጋት ጉብኝት እና ምስተግዶ

በኪሪያት ጋት የምናደርጋቸው ጉብኝቶች የተለያዩ እና አንዳቸው ከሌላው የተለዩ ናቸው ፡፡ በሱዳን ለሞቱ የመታሰቢያ ሐውልት ላይ የሚተረክ የግል ታሪክን የሚያጣምሩ ጉብኝቶች አሉ ፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ማህበረሰብ ፀሎት ቤት የሚያስቃኝ ጉብኝት አለ ፡፡ በተጨማሪም ፣ ከቄሶች እና ከማህበረሰቡ ቁልፍ ሰዎች ጋር ስብሰባዎች እንዲካሄዱ ጥረት እናደርጋለን፡፡

ደንበኞች ይመክራሉ

አግኙን

መገኛችን
ማህበራዊ አውታረ መረቦች

ማሳጅ መላክ

ንግግሮችን ፣ አውደ ጥናቶችን እና እንቅስቃሴዎችን ለማዘዝ በቅጽ ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊያነጋግሩን ይችላሉ በቅርቡም ወደ እርስዎ እንመለሳለን

Scroll to Top