הקס

ሰራተኞቹ

ሃራብ አዛርያ ፍትጉ

የ 39 ዓመቱ ሃራብ አዛርያ ፍትጉ የወ/ሮ ሚርያም ባለቤት እና የ 8 ልጆች አባት ናቸው ፡፡ "ተዋጊው፣ ቄስ እና አምስቱ የስሜት ህዋሳት” የተሰኘውን ፕሮጀክት ያዳብራል ፣ ያስተዳድራል ፣ በትምህርት የሁለተኛ ድግሪ ምሩቅ፣ የቡድን አስተባባሪ ፣ ማህበራዊ ታጋይ ፣ የአየር ወለድ ተዋጊ የበሩ ፣ የመንፈሳዊ መሪ የቄስብርሃኑ ፍትጉ ልጅ ፡፡ በ 10 ዓመታቸው ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የገቡ እና የኢትዮጵያ ይሁዲዎች የተሳካ ውህደታቸውን ለማጥለቅ እና በእስራኤል ህብረተሰብ ውስጥ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እሴቶችን ቦታ እንዲኖራቸው የሚሰሩ ናቸው ፡፡ በኪሪያት ጋት ከተማ ውስጥ የግብርና እርሻውን ሃሳብ ያፈለቁ እና ለ 10 ዓመታት ያህል ያስተዳደሩ ናቸው ፡፡

ቂስ ምንተስኖት ወንዴ

የ 55 ዓመቱ ቄስ ምንተስኖት ወንዴ የወ/ሮ ሊያ ባለቤት እና የ 11 ልጆች አባት ናቸው ፡፡ ንግግሮች እና "ተዋጊው፣ ቄስ እና አምስቱ የስሜት ህዋሳት" ፕሮጀክት በቅርብ ያማክራሉ፡፡በቄስነት ያገለግላሉ፡፡በኪርያት ጋት እና በላሂሽ ሻፊር የክልል ሰፈሮች የመንፈሳዊ እና ማህበራዊ መሪ ሆነው ያገለግላሉ ፡፡ ከሊቀ ካሃናት (ቄስ) ምናሴ ዝምሩ ነ/ይ ለ 12 ዓመታት ቅስና የተማሩ ሲሆኑ እስከ መጨረሻው ቀናቸው ድረስ የቄሱንበክብር አገልግለዋል ወይም ተከባክበዋል፡፡ የፀሎት መፀሐፍ በግዕዝ ቋንቋ ለመጀምሪያ ጊዜ የፃፉ፡፡ በኪሪያት ኦኖ ኮሌጅ የአንደኛ ድግሪ ተማሪ እና የኢዮጵያ ይሁዲዎች የሊቀ ከሃናት ሀገር አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት አባል ናቸው፡፡

ዶ / ር ሽራ ቡህሪስ-ባዛክ፡፡

ዶ / ር ሽራ ቡህሪስ-ባዛክ የአቶ ኖዓም ባለቤት እና የሰባት ልጆች እናት ናቸው፡፡ "የቄስ ፣ ተዋጊው እና በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት" የቅርብ አማካሪ ናቸው ፣ የዩኒቨርስቲ መምህር እና በማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ የትምህርት ሚኒስትር አማካሪ እና በትምህርት ሚኒስቴር ለአስር ዓመታት ያገለገሉ፣ በኪሪያት ጋት የባህል እድገትን የሚያጠናክር ድርጅት የመሰረቱ እና የአስተዳደሩ፣ ‹ማሪያን ማእከል› የቦርድ አባል በመሆን ያገለገሉ ናቸው፡፡

አለሙ ንጋቱ

የ 45 ዓመቱአለሙ ነጋቱ የወ/ሮ ሾሽ ባለቤት እና የ 4 ልጆች አባት ናቸው፡፡ "የቄስ ፣ ተዋጊው እና በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት" አስተማሪ ናቸው፡፡ በኤሌክትሪክ ምህንድስና ዲፕሎማ ያላቸው ሲሆን በያቭኔ ከተማ ውስጥ የሲኤምኤምአይ ማሽኖችን በሚያመርት ድርጅት እንደ ተቆጣጣሪ ሆነው ይሠራሉ ፡፡ በያቭኔ የሃይማኖት ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ በኢትዮጵያ ተምረዋል ፡፡ በጣም በጥሩ ደረጃ አማርኛን ያነባሉ ይፅፋሉ፡፡ በ 16 ዓመታቸው ወደ እስራኤል የመጡ ፣ ከቄስ ቤተሰብ የተወለዱ ፣ በያቭኔ የኢትዮጵያን ማህበረሰብ እድገትና ስኬታማነት ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ናቸው ፡፡

አረጊቱ ከበደ

አረጊቱ ከበደ የአቶ ወርቁ ባለቤት እና የ 5 ልጆች እናት ናቸው ፡፡ "የቄስ ፣ ተዋጊው እና በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት" አስተማሪ ናቸው፡፡ የአንደኛ ድግሪ ምሩቅ እና በኢትዮጵያ የሂሳብ እና የአማርኛ ትምህርቶችን ያስተማሩ ሲሆን በእስራኤል ሀገር ለ 17 ዓመታት በትምህርት መ/ቤት የ5 ኛ ነጥብ ተማሪዎች ለፈተና ያቀረቡ፣ የማህበርሰብ ታጋይ፣ በክሪያት ጋት "መሰረት" የተባለውን የሕይወት ታሪክ ጽሑፎችን በማዘጋጀት ለተውኔት በማቅረብ የማህበረሰቡን ችግሮች በተውኔት የሚያሳይ ማህበራዊ ፕሮጀክት ከመሰረቱ መካከል አንዱ ናቸው፡፡

አግኙን

መገኛችን
ማህበራዊ አውታረ መረቦች

ማሳጅ መላክ

ንግግሮችን ፣ አውደ ጥናቶችን እና እንቅስቃሴዎችን ለማዘዝ በቅጽ ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊያነጋግሩን ይችላሉ በቅርቡም ወደ እርስዎ እንመለሳለን

Scroll to Top