הקס

ስለ ፕሮጀክቱ

"ቄስ፣ ተዋጊው እና አምስቱ ህዋሳት" ማህበራዊ ድርጅት ሲሆን ዓላማውም ለወጣቶች ፣ ለወላጆች እና ለሌሎችም የትምህርት እና የእሴት ባህሪያትን ማበርከት ወይም ማቅረብ ነው፡፡ምክንያቱም የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እሴቶች እና ባህልን ማጤን እና ማወቅ የዘረኝነትን ክስተት ለማጥፋት ፣ በህብረተሰባችን ውስጥ መቻቻልን ለማጠንከር ፣ አንዱ ሌላውን የመቀበል ማህበራዊ አቅም ለማዳበር እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁሉም ሰው በደህንነት ስሜት የሚኖርበትን ቦታ መመስረት እንድንችል ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብለን እናምናለን፡፡
ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 41 ቁጥር 6 እንደ ተፃፈው “ሁሉም እያንዳንዱ ባልንጀራውን ይረዳው ነበር፥ ወንድሙንም፦ አይዞህ ይለው ነበር”፡፡

የእኛ ፕሮጀክ ሃሳብ የተወለደው የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን እሴቶች እና ጥንካሬዎች በእስራኤል ህብረተሰብ ውስጥ ሰርጠው እንዲገቡ ለማድረግ ካለን ፍላጎት እና ካለው አስፈላጊነት የተነሳ ነው፡፡ህብረተሰባችንከሁሉም የእስራኤል ህብረተሰብ ጋር እንዲዋህድ ማገዝ እንፈልጋለን ይህንም የምናደርገው የህብረተሰባችን ወግና ባህል ለሁሉም የእስራኤል ህብረተሰብ በማስተዋወቅ እና ተደራሽ በማድረግ ይሆናል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ይሁዲዎች ማህበረሰብ ላይ የዘረኝነት እና የመድልዎ ክስተት ይቀንሳል፡፡ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች አምስቱን የስሜት ህዋሳትን በመጠቀም ሲሆሆን፤ ማለትም፥ መስማት ፣ መቅመስ ፣ ማሽተት ፣ ማየት እና መንካት እነዚህን በመጠቀም በተሞክሮ እና ዋጋ-ተኮር በሆነ መንገድ የሚተላለፉ ናቸው፡፡
ፕሮጀክቱ የተቋቋመው የቅርያት ጋት ነዋሪ በሆነው እና የ 8 ልጆች አባት በሆነው በራብ አዛሪያ ፍትጉነው ፡፡ አዛርያ ይህን ፕሮጀክት የመሰረተው የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ባህልን ወግ ለመላው እስራኤል ህዝብ በማስተላለፍ በሁለቱ መካከል ጥሩ ግንኙነት ወይም ውህደት ለመፍጠር ካለው ከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት ሲሆን በዚህ ተግባሩ የአባቱን የቄስ ብርሃኑ ፍትጉ ነፍስ ይማር ትዕዛዛም ፈፅሟል፡፡ ቄስ ብርሃኑ ፍትጉ ገና በወጣትነቱ ጀምሮ ቀላል ነው ከባድ ነው ሳይል የቤተሰቡን ባህል እና ወግ ከኢትዮጵያጀምሮ የሚጠብቅና የሚያከብር ነበረ፡፡

ስለ ቄስ ባርሃኑ ፍትጉ በትንሹ

ቄስ ብርሃኑ ፍትጉ ነ/ይ በወጣትነታቸው በመረባ የሚኖሩ የቤተ እስራኤል ማህበረሰብን በመንፈሳዊ/ ሃይማኖታዊ መሪ እና አስተማሪ ነበሩ፡፡
እ.ኤ.አ. በ 1991 ወደ እስራኤል ከገቡ በኋላም ቢሆን በሁሉም ሥነ-ሥርዓቶች እና በማህበረሰብ ዝግጅቶች በመገኘት ማህበረሰቡን ማገልገሉን ቀጥሏል ፣ የማህበረሰባዊ ጉዳዮችን ፣ የግል ዝግጅቶችን እና ሌሎችንም ጉዳዮች በተመለከተ ለሁሉም የፓርዴስ ሀና-ካርኩር ማህበረሰብ አባላት እና በአጠቃላይ ሁሉንም በምክር አገልግለዋል፡፡ በህይወታቸውየመጨረሻ አሥራ አንድ ዓመታት ውስጥ እንኳን ታመው እና በሳምንት 3 ጊዜ የእንኩላሊት እጥባት እያደረጉ እጅግ ቢደክማቸውም ለማህበረሰብ ዝግጅቶች ሲጋበዝ መሄዳቸውን አላቆሙም ነበር ፡፡ በዝግጅቱ ላይ ቄስ ካልተገኘ በህብረተሰቡ ዘንድ እንደሚታወቀው የዝግጅቱ ትርጉም የለሽ ስለሚሆን ህብረተሰቡ ደስተኛ እንዲሆን በማለት ማናቸውም ዝግጅቶች በመሄድ ለዝግጅቱ ባለቤቶች ክብር ይሰጣሉ ፡፡

ቄስ ብርሃኑ ፍትጉ ባለ ጥሩ ስነ ምግባር ሰው ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 1994 የእስራኤል መንግስት የኢትዮጵያን ይሁዲዎች ደም ወደ ቆሻሻ በመድፋቱ ምክንያት የተካሄደን ትልቅ ሰልፍ ተከትሎ መንግስት በሰልፉ ላይ ቄሶች ከሃይማኖት ጉዳይ መስሪያ ቤት ወረሃዊ ደሞዝ እንደሚቆረጥላቸው ቢያውጅም ቄስ ብርሃኑ ፍትጉ በጭራሽ ከራባኖት ገንዘብ ለመውሰድ ጭራሽ ፈቃደኛ አልነበሩም፣ ሁሉም ቄሶች ወራዊ ደሞዙን ሲቀበሉ ቄስ ብርሃኑ ደሞዙን ካልተቀበሉ ትቂት ቄሶች አንዱ ነበሩ፡፡ በቢቱዋህ ለኦሚ የሚቀበሏት ትንሽ ገንዘብ ይበቃኛል ብለዋል፡፡ እኛም ልጆች ወደ ሃይማኖት ጉዳይ መስሪያ ቤት ስናመለክት አባታችን ፎርሙን መሙላት ብቻ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሮናል ፡፡ ምንም እንኳን ወዳጅ ጓደኞቻቸው ደሞዙን እንዲቀበሉ ብዙ ለማሳመን ቢሞክሩም መስሪያ ቤቱ የሃይማኖት መሪዎች ስለ መሆናችን እውቅና ካልሰጠን ምንም አይነት ገንዘብ አልቀበልም በማለት በአቋማቸው ፀንተው አልፈዋል፡፡ ስለሆነም ለ 26 ዓመታት ከሁሉም ማህበራዊ ሁኔታዎች ጋር የተከበረ ደመወዝ መቀበል ሲችሉ በዚህ ፈንታ ማህበረሰቡን በንፁህ ልብ እና በተልዕኮ ስሜት ማገልገልን መርጠዋል፡፡
ቄስ ብርሃኑ ፍትጉ ለእስራኤል 50ኛ የነፃነት ቀን ክብር ችቦአብርተዋል፡፡ ይህም የፓርድስ ሃና ካርኩር ለሚኖሩ 300 የኢትዮጵያ ይሁዳውያን ቤተሰብ የሃይማኖት መሪ እና ተወካይ እንድሁም የማህበረሰቡ የችግር ፈች ታጋይ በመሆናቸው ነው፡፡

የፕሮጅርክቱ ግቦች ምንድን ናቸው?

  • በእስራኤል ህብረተሰብ ውስጥ የኢትዮጵያ ይሁዲዎች እሴቶች እና ቅርሶችን ማዋሃድ፡፡
  • ስለ ኢትዮጵያ ይሁዎች የአሉትን የተሳሳቱ አመለካከቶች ማስወገድ፡፡
  • ተሳታፊዎችን በኢትዮጵያ ይሁዲዎች እሴቶች፣ ባህሎችና ቅርሶች ማበልፀግ፡፡
  • የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባህልና ወግ በሰነድ መዝግቦ ማቆየት፡፡

የስሙ ትርጉም “ቄስ ፣ ተዋጊው እና አምስቱ የስሜት ህዋሳት”

ቄስ – ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ባህልና ወግ እውቅና ማዳበር አላማ ያደረገ ነው እና ቄሶች የራባናትን ቦታ የያዙ ስለሆኑ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ መሪዎች ናቸው፡፡

ተዋጊው – ፕሮጀክቱ ከአሉት አላማዎች አንዱ ለፕሮጀክቱ ተሳታፊዎች በጓደኛማቾች እና በወታደሮች መካከል የሚሰማውን ተመሳሳይ ስሜት ማስተላለፍ ነው ፡፡ በጦር ሜዳ አብረው በተዋጉ ተዋጊዎች መካከል የሚፈጠረው የአድነት ወይም ጓደኝነት ትስስር እጅግ ጠንካራ ነው "አንዱ ለሁሉም፣ ለሁሉም ለአንድ” ይህ ስሜት ምን አልባት ተራ ስሜት ሊመስል ይችላል ነገር ግን የተዋጊዎች የጓደኝነት ትስስር ከዚህ በላይ ነው ፡፡ ከተዋጊዎች የሚጠየቀው ታማኝነት እና የጋራ ዋስትና እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ የቤተሰብ አባላት ካልሆኑ ወይም የትዳር ጓደኛ ውጭ የማይታይ የማይሰማ ነው፡፡ ስለዚህ ፣ በእኛ ዘንድ ተዋጊው በኅብረተሰቡ ውስጥ መሆን ላለበት መልካም ነገር ተምሳሌ ነው፡፡ እንዲሁ በፕሮጀክቱ ይዘቶች ውስጥ የተሰመረበት የእስራኤል ህዝብ እንደ ሀገር የሚኖረው የመልክ እና የመነሻ ልዩነት ሳይኖር ሁሉንም ክፍሎቹን መቀበል ወይም በማቀፍ ብቻ ነው ፡፡

እናም አምስቱ የስሜት ህዋሳት – በፕሮጀክቱ ሂደት ሁሉ መልእክቶቹ በተሳታፊዎች ዘንድ ዕውቀትን እና ልምድን ለማስቀረት በሚረዳ መንገድ አምስት ህዋሳቶችን በመጠቀም በቡድን እና አስደሳች ተሞክሮን በሚያጣምር መንገድ ይተላለፋሉ፡፡

አግኙን

መገኛችን
ማህበራዊ አውታረ መረቦች

ማሳጅ መላክ

ንግግሮችን ፣ አውደ ጥናቶችን እና እንቅስቃሴዎችን ለማዘዝ በቅጽ ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊያነጋግሩን ይችላሉ በቅርቡም ወደ እርስዎ እንመለሳለን

Scroll to Top