הקס

ምን ዓይነት ትምህርት አዘል እንቅስቃሴዎችን እናቀርባለን?

ገለፃዎች

ከኢትዮጵያ ይሁዲዎች ባህል እና ታሪክ ጋር የሚያስተዋውቁ ትምህርቶችን እንሰጣለን ፡፡

የግል ታሪክ

የግል የሕይወት ታሪኮች እና ወደ እስራኤል ለመግባት የተደረገውን የጉዞ ታሪክበኢትዮጵያ ሲኖሩ በነበሩ፣ የጉዞው ስቃይ በአሳለፉ እና ወደ እስራኤል ምድር እስኪደርሱ ድረስ የጉዞውን አስቸጋሪ ውጣ ውረድ ባሳለፉ ሰዎች እናቀርባለን

የሸክላ ቁሳቁሶች ዝግጅት

የተለያዩ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን በሸክላ ማዘጋጀት። በዝግጅቱሂደት የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ከእጅ ስራ ጋርያላቸውን ታሪካዊ ይዘት በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

ማህበረሰባዊ መዝናኛ

ለወላጆች እና ለልጆችየኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ይዘት መሰረት ያደረጋ ልዩ ጊዜ ማሳለፍ በተለይም በበዓላት እና በእረፍት ጊዜ፡፡

በአባባሎች ዙሪያ

አባባሎችን በመጠቀም የኢትዮጵያ ይሁዲዎች ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶች መማር፡፡

በአማርኛ መጻፍ

የስነ ጥበብ ሥራዎችን ፡፡ ተሳታፊዎች ስማቸውን በአማርኛ መጻፍ ይማራሉ እንዲሁም ስማቸውበአማርኛ እና በሌላ ቋንቋ የተጻፈበት፡ ለበር ምልክት የሚሆን ይሰጣቸዋል፡፡

በበዓላት ዙሪያ የሚከናወኑ ተግባራት

በእስራኤል በዓላት እና ለኢትዮጵያውያን ይሁዳዎች ብቻ የሚከበሩ በዓላትን የማሳወቅ እና በአሁኑ ጊዜ ከሚከበሩት በዓላት ጋር የማነፃፀር አዝናኝ ትምህርት፡፡

የስግድ በዓል

ስለ ስግድ በዓል፡ መነሻ የትምህርት ንግግር፡፡ በኢትዮጵያ ስለ ነበረው አከባበር የግል ታሪክ፣ስለ በዓሉ ወግ እና ደምብ እንዲሁም ድሮ እንዴት ሲከበር እንደነበር እና ዛሬ እንዴት እንደሚከበር ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብ ትውውቅ

የዳቦ እና አንጅራ ዝግጅትን ጨምሮ በልዩ ንጥረ ነገሮች የተዋህደ ባህላዊ ምግብን ማዘጋጀት እና በመጨረሻም የተዘጋጀውን ምግብ መቅመስ፡፡

ባህላዊ “የእስክስታ” ውዝዋዜ

እስክስታ የሚለው ቃል “የትከሻ ዳንስ” የሚል ነው ፡፡ እስክስታውየሚደረገው ተስማሚ በሆነ የሙዚቃ ሪትም ሲሆን የሙዚቃውን ሂደት በመጠበቅ በአንገት በትክሻ እና በደረት የሚጭፈር ነው ፡፡ ጭፈራው ልዩ ኃይል ያለው ጭፈራ ነው፡፡

ራስን ፎቶ ማንሳት

በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ/ዝግጅት መጨረሻ ላይ የነበረውን ክንዋኔ ከሚያሳየው የገጠር መልክዓ ምድር ዳራ ጋር እንዲሁም የኢትዮጵያዊያን በባህላዊልብስ በመልበስእራስን ፎቶግራፍ ማንሳት ይችላሉ ፡፡

ባህላዊ እና ታሪካዊ ተዕይንት

በእያንዳንዱ ዝግጅትየተለያዩ ቁሳቁሶችእና ባህላዊ ልብሶች ያካተተ ተዕይንት ማቅረብ ይቻላል፡፡

አግኙን

መገኛችን
ማህበራዊ አውታረ መረቦች

ማሳጅ መላክ

ንግግሮችን ፣ አውደ ጥናቶችን እና እንቅስቃሴዎችን ለማዘዝ በቅጽ ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊያነጋግሩን ይችላሉ በቅርቡም ወደ እርስዎ እንመለሳለን

Scroll to Top