הקס

በክሪያት ጋት ጉብኝት እና ምስተግዶ

በኪሪያት ጋት የምናደርጋቸው ጉብኝቶች የተለያዩ እና አንዳቸው ከሌላው የተለዩ ናቸው ፡፡ በሱዳን ለሞቱ የመታሰቢያ ሐውልት ላይ የሚተረክ የግል ታሪክን የሚያጣምሩ ጉብኝቶች አሉ ፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ ይሁዲዎችን ማህበረሰብ ፀሎት ቤት የሚያስቃኝ ጉብኝት አለ ፡፡ በተጨማሪም ፣ ከቄሶች እና ከማህበረሰቡ ቁልፍ ሰዎች ጋር ስብሰባዎች እንዲካሄዱ ጥረት እናደርጋለን፡፡

ከእነዚህ ጉብኝቶች በተጨማሪ ለቡድኖች የአርብ እና የቅዳሜ መስተግዶዎችን እናደርጋለን፡፡ እንግዶች በቂሪያት ጋት ከተማ ከሚገኙ ቤተሰቦች ዘንድየኢትዮጵያን ባህላዊ ምግብ ይመገባሉ
፡፡ በተጨማሪም ፣ ከቄሶች ጋር እጅግ ልዩ እና አስደሳች የሆኑ የፀሎት ስነ ሥርዓቶችን እናካሄዳለን፡፡ በመጨረሻም፣ በአካባቢያችን ካሉ ቁልፍ የማህበረሰቡ ሰዎች ጋር የማይረሳ እና ልዩ ስሜት የሚሰጥ ግንኙነት እናደርጋለን፡፡

በጉብኝቶቹ አማካኝነት ተሳታፊዎች እና እንግዶች እጅግ በጣም አስደሳች በሆነ መንገድ የህብረተሰቡን ትክክለኛ የአኗኗር ዘይቤ ጠለቅ ብለው እንዲያውቁ እና እንዲሞክሩ እናደርጋለን፡፡ ተሳታፊዎች በህይወት ዘመናቸው ለአንድ ብቻ የሚያገኙት አስደሳች ነገር፣ ባህላዊ ልብሶችን መልበስ ፣ በግዕዝ ቋንቋ በሚማርክ ፀሎት ቤት ውስጥ ከቄሶች ጋር መጸለይ ፣ ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ዘንድ መስተናገድ፣ ከሁሉም የቤተሰብ አባል ጋር የግል ግንኙነት መፍጠር እንዲሁም በሰንበት ቀን ባህላዊ የኢትዮጵያን ምግብንመመገብን ያካትታል፡፡

አግኙን

መገኛችን
ማህበራዊ አውታረ መረቦች

ማሳጅ መላክ

ንግግሮችን ፣ አውደ ጥናቶችን እና እንቅስቃሴዎችን ለማዘዝ በቅጽ ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊያነጋግሩን ይችላሉ በቅርቡም ወደ እርስዎ እንመለሳለን

Scroll to Top